የግብፅ ቱሪዝም እና አርኪኦሎጂ ሚኒስቴር በአሌክሳንድሪያ አዳዲስ ጥንታዊ ቅርሶችን ይፋ አደረገ
19:20 02.05.2026 (የተሻሻለ: 20:34 02.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የግብፅ ቱሪዝም እና አርኪኦሎጂ ሚኒስቴር በአሌክሳንድሪያ አዳዲስ ጥንታዊ ቅርሶችን ይፋ አደረገ
የግብፅ የአርኪኦሎጂ ዘርፍ ኃላፊ መሐመድ አብደል-ባዲ፤ ግኝቶቹ በጥንታዊቷ ከተማ የነበረውን የመኖሪያ እና የአገልግሎት ግንባታ የዕድገት ሂደት የሚያሳዩ አጠቃላይ ሞዴል መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከተገኙት ቅርሶች መካከል፦
🟠 ከኋለኛው የባይዛንታይን ዘመን የተገኙ ባለ ክብ ቅርጽ የሕዝብ መታጠቢያ ቤቶች፣
🟠 በሞዛይክ ወለል ያጌጠ የመኖሪያ ቪላ፣
🟠 የላቁ የውሃ አቅርቦት እና አስተዳደር መሠረተ ልማቶች፣
🟠 የባከስ፣ የአስክለፒየስ እና አንገቱ የተቆረጠ የሚነርቫ እብነ በረድ ሐውልቶች፣
🟠 ጥንታዊ ሳንቲሞች፣ ማሰሮዎች፣ የሸክላ ውጤቶች እና የታሸጉ የአምፎራ ስብርባሪዎች ይገኙበታል።
ይህ ግኝት ለአሌክሳንድሪያ አርኪኦሎጂያዊ ታሪክ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን የገለጹት የቱሪዝም እና አርኪኦሎጂ ሚኒስትሩ ሸሪፍ ፋቲ፤ ከተማዋ ከጥንቱ ዓለም ግንባር ቀደም የባሕል ማዕከላት አንዷ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X