የመንግሥትን የዕለታዊ ሥራ አፈጻጸም የሚቆጣጠር የዲጂታል ሥርዓት ሊዘረጋ ነው

ሰብስክራይብ

የመንግሥትን የዕለታዊ ሥራ አፈጻጸም የሚቆጣጠር የዲጂታል ሥርዓት ሊዘረጋ ነው

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሹመኞች እና ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን በዲጅታል መንገድ መቆጣጠር ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።

ሥርዓቱ ሥራዎችን "የተሳኩ"፣ "ያልተሳኩ"፣ “በቀጣይ የሚከናወኑ” በማለት በዝርዝር የሚያሳይ መረጃ እንደሚይዝ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ተናግረዋል።

ሚኒስትሮች፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች የተቋሞቻቸውን አፈጻጸም በቅርበት እንዲከታተሉ ያግዛልም ተብሏል።

አሠራሩ “በተቋማት ውስጥ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና በውጤት ላይ የተመሠረተ ግብረ መልስ ለመስጠት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል” ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0