የዓለም የኃይል ሚዛን ዳግም እየተዋቀረ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት አየተነሳ ያለበት ጊዜ ላይ ነን - ኢትዮጵያዊ ምሁር
16:21 02.05.2026 (የተሻሻለ: 16:38 02.05.2026)

ሰብስክራይብ
የዓለም የኃይል ሚዛን ዳግም እየተዋቀረ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት አየተነሳ ያለበት ጊዜ ላይ ነን - ኢትዮጵያዊ ምሁር
ወቅታዊ ጦርነቶች፣ የኒውክሌር ጉዳይ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች በዓለም አዲስ የኃይል አሰላለፍ እና ምድብ እንዲፈጠር እያደረጉ እንደሚገኙ የፖሊሲ አማካሪ እና የኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ለዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ከዚህ በኋላ በዓለም ጉዳይ በብቸኝነት የምትወስነው አሜሪካ ብቻ አትሆንም።
"ከዶላር ውጪ መገበያየት አሁን እየሄደበት ባለበት ፍጥነት በእኛ የህይወት ዘመን የዶላር የበላይነት እየቀነሰ ሲሄድ እናያለን። ይህ ከዩናይትድ ስቴትስ ባሻገር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሌሎች ኃይሎች እና የኃይል ማዕከላት ይመጣሉ ማለት ነው። አሁን የምናየው የዓለም ኃይል በምዕራብ፣ በሰሜን እና በደቡብ በኩል ዳግም ሲዋቀር ነው።"
እንደ ምሁሩ ገለፃ፤ ለቅኝ አገዛዝ፣ ለኢኮኖሚ ብዝበዛ እና ለባሕል መጥፋት ተጠያቂ የሆነው የምዕራቡ ዓለም ጥምረት መዳከም ለደቡባዊ የዓለም ክፍል እፎይታን የሚሰጥ ነው።
"የምዕራቡ ዓለም ጥምረት ሙሉ በሙሉ ፈርሷል። ይህ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ዘመን የብሪክስ ጥምረት ይፈልገው የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ለዓለም ከሰማይ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ የባርነት፣ ቅኝ አገዛዝ እና የዓለም ኢኮኖሚ እና ባሕል ውቅርን የማውደም ታሪክ ያለው የምዕራቡ ዓለም አሁን ከደቡቡ ዓለም ገሸሽ የሚልበት ግዜ ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X