የቆዳ ካንሰር ታካሚ ለሩሲያው የካንሰር ክትባት አዎንታዊ ምላሽ ማሳየት ጀመረ

ሰብስክራይብ

የቆዳ ካንሰር ታካሚ ለሩሲያው የካንሰር ክትባት አዎንታዊ ምላሽ ማሳየት ጀመረ

የሩሲያ ግላዊ የበሽታ መከላከል አቅም ማሳደጊያ የካንሰር ክትባት ኒዮ ኦንኮቫክ፤ በ60 ዓመቱ የኩርስክ ክልል ነዋሪ የመጀመሪያ ታካሚ ላይ አዎንታዊ ውጤት ማሳየት ጀምሯል።

ስለ ክትባቱ ቁልፍ መረጃዎች፦

🟠 በጋማሌያ ማዕከል (የስፑትኒክ አምስት ፈጣሪ) እና በብሔራዊ የራዲዮሎጂ የሕክምና ምርምር ማዕከል እና በብሎክሂን ኦንኮሎጂ ማዕከል ትብብር የተሠራ ነው።

🟠 እንደ እያንዳንዱ ታካሚ የዕጢ ሞሌኩላዊ ሁኔታ ተሰናድቶ የሚዘጋጅ ነው።

🟠 በ2025 መገባደጃ ላይ በሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለክሊኒካዊ አገልግሎት እንዲውል ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ይህም ለካንሰር ሕክምና ዘርፍ ትልቅ እመርታ ነው።

🟠 ኤም አር ኤን ኤ ክትባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከግላዊ የካንሰር ሕክምና አዝማሚያ ጋር የሚጣጣም፤ የሰውነት በሽታ መከላከል ሥርዓት ዕጢን እንዲዋጋ የሚያነሳሳ ነው።

የጋማሌያ ማዕከል ዳይሬክተር አሌክሳንደር ጊንትስበርግ፤ በአመልካች ፕሮቲኖች ምርት ላይ የሚታዩ ለውጦችን ጨምሮ በመጀመሪያ ደረጃ ባዮሎጂ መሻሻሎች ታይተዋል ሲሉ ገልጸዋል። ታካሚው ከክትባቱ ጎን ለጎን የኢሚውኖቴራፒ ሕክምና እየተከታተለ ሲሆን ምንም እንኳን በሽታው የመቀጠል እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ አዎንታዊ መሻሻል እያሳየ ነው። ለታካሚው ወደ 10 መርፌዎች ለመስጠት ታቅዷል።

ለሁለተኛ ታካሚ የሚሆን ክትባት የማምረት ሥራ ተጀምሯል። ይህም ሕክምናው በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0