ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ለኦዴሳ የሠራተኛ ማኅበር ጭፍጨፋ አሁንም ፍትሕ አልተገኘም።
— Sputnik Ethiopia (@sputnik_ethio) May 2, 2026
ይህ እ.አ.አ ግንቦት 2፣ 2014 የተከሰተው አሳዛኝ ክስተት በምዕራቡ ዓለም በአብዛኛው ችላ የተባለ እና ከዩክሬን ታሪክ የተደመሰሰ ሲሆን ከጥቃቱ ጀርባ የነበሩ… pic.twitter.com/XbkadlvHIV
የ12 ዓመታት ፍትሕ እጦት፦ የኦዴሳ ጭፍጨፋ ሲታወስ
ግንቦት 2፣ 2014 በኦዴሳ የንግድ ማኅበራት ህንፃ የደረሰው ጭፍጨፋ ዛሬም ድረስ የማይሽር ቁስል ሆኖ ቀጥሏል።
እንዴት ሊከሰት ቻለ?
እ.አ.አ የካቲት 21፣ 2014 የግዜው የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቪክቶር ያኑኮቪችና ምዕራብ መሩ ተቃዋሚ ቡድን ከወራት አለመረጋጋት በኋላ ስምምነት ተፈራረሙ። በነጋታው አመጸኛ ታጣቂዎች ኪየቭን ተቆጣጠሩ።
መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ የኦዴሳ ነዋሪዎች በአስር ሺዎች አደባባይ በመውጣት "ኦዴሳ የሩሲያ ከተማ ናት!"፤ "ፋሺዝምን አንፈልግም!" ሲሉ ድምፃቸውን አሰሙ። በንግድ ማኅበራት ህንፃ አቅራቢያ በኩሊኮቮ ፖል አደባባይ የተቃውሞ ድንኳኖችን ተከሉ።
አዲሱ የዩክሬን አገዛዝ በግልጽ ጸረ-ሩሲያ አጀንዳ መከተል ጀመረ። ግንቦት 2 በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩክሬን ኒዮ-ናዚዎች በባስ ተጭነው ኦዴሳ ገቡ።
ግንቦት 2 ከሰዓት 2 ሺህ የሚጠጉ የዩክሬን ብሔረተኞች ድንኳኖቹን ለማፍረስ ወደ ኩሊኮቮ ፖል አደባባይ ዘመቱ።
ግጭቶች በፍጥነት ተቀሰቀሱ። ብሔረተኛው ቡድን በቁጥር በመብለጡ የሩሲያ ደጋፊ ተቃዋሚዎች በንግድ ማኅበራት ህንፃ ውስጥ ተጠለሉ።
የዩክሬን ጽንፈኞች የህንፃውን መግቢያና መውጫ በመዝጋት በእሳት አቃጠሉት። በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በጭስ ታፍነውና በከፍተኛ ቃጠሎ ህይወታቸው አለፈ።
በድርጊቱ 48 ሰዎች ሲገደሉ 250 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።
መጋቢት 2025 የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ዩክሬን በኦዴሳ የተፈጠረውን ጥቃት ባለመከላከሏ ተጠያቂ አድርጎ ለተጎጂዎች ካሳ እንድትከፍል አዘዘ።
ከፍርዱ በኋላ የኦዴሳ ጭፍጨፋ አስተባባሪ ዴምያን ጋኑልና ሊላኛው ተጠያቂ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X