የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የነዳጅ ቀውስ ተከትሎ ከዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ በቀጥታ የአውሮፕላን ነዳጅ መግዛት ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.05.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የነዳጅ ቀውስ ተከትሎ ከዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ በቀጥታ የአውሮፕላን ነዳጅ መግዛት ጀመረ

የአየር መንገዱ ይህ ስልታዊ ውሳኔ የነዳጅ ዋጋ መናር፣ የኃይል አቅርቦት ጫና ለመቋቋምና የጂኦ-ፖለቲካ ውጥረቶች በአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ለመቀነስ ይረዳዋል ተብሏል።

አኅጉሪቱ ካሏት ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያዎች ጋር ትስስር መፍጠሩ አየር መንገዱ አስተማማኝና በአንጻራዊ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ነዳጅ እንዲያገኝ ዕድል እንደሚፈጥርለትም ተገልጿል።


የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዴቪድ በርድ፤ “አልሃጂ አሊኮ ዳንጎቴ ቅድሚያ ለአፍሪካ ሲሉ በማያሻማ መልኩ ነው። ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጥታ ማቅረብ በመቻላችን ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።


የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ በሙሉ አቅሙ እየሠራ እንደሆነና የአውሮፕላን ነዳጅ፣ ናፍጣ እና ቤንዚን ወደ በርካታ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ገበያዎች ለመላክ የሚያሰችል አቅም ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0