ዩኤኢ “በፈተናዎች ወቅት ጭምር ከኢትዮጵያ ጎን ያልተለየች የቁርጥ ቀን ወዳጅ” ሀገር ናት - የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ዩኤኢ “በፈተናዎች ወቅት ጭምር ከኢትዮጵያ ጎን ያልተለየች የቁርጥ ቀን ወዳጅ” ሀገር ናት - የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር

‍‍ ይህ የተባለው የሼክ ዛይድ የበጎ አድራጎት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ እንደሆነ ይፋ በተደረገበት ሁነት ነው።

ውድድሩ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም “ለደግነት እንሩጥ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ መክዩ መሀመድ፤ “ውድድሩ ሰብዓዊነትን ከመደገፍ ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በተለይም የስፖርት ዲፕሎማሲን የበለጠ ያጠናክራል” ብለዋል።

ውድድሩ ከኤሚሬቶች የመጡ 50 ተሳታፊዎችንና በልዩ ሁኔታ የሚጋበዙ ታዋቂ አትሌቶችን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችንና ባለሀብቶችን ጨምሮ 4 ሺህ 500 ገደማ ሰዎችን እንደሚያሳትፍ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0