የማሊ ፕሬዚዳንት አሲሚ ጎይታ አዲሱን የማሊ የመከላከያ ስትራቴጂ ይፋ አደረጉ
18:13 01.05.2026 (የተሻሻለ: 18:14 01.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማሊ ፕሬዚዳንት አሲሚ ጎይታ አዲሱን የማሊ የመከላከያ ስትራቴጂ ይፋ አደረጉ
መሪው "ብሔራዊ የመከላከያ እና የደህንነት ማዕቀፉን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ 16 ስልታዊ መመሪያዎችን አውጥተዋል" ሲል የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።
ዕቅዱ የቀረበው በከፍተኛው የብሔራዊ መከላከያ ምክር ቤት ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ መመሪያዎቹ የሚከተሉትን ዓላማዎች ያነገቡ ናቸው፦
▪ በመላ ሀገሪቱ ያለውን የደህንነት ሽፋን ማጠናከር፣
▪ የታለሙ የጥቃት ዘመቻዎችን ማበርታት፣
▪ የኦፕሬሽን የደህንነት መረጃ አሰባሰብን ማሻሻል፣
▪ በተለያዩ የጦር ኃይሎች መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር፣
▪ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ያለውን ትብብር ማሳደግ።
በምክክሩ ወቅት ምክር ቤቱ በሀገሪቱ የደህንነት ሁኔታ ላይ "ጥልቅ ትንታኔ ማካሄዱን" መግለጫው አመልክቷል።
ሚያዝያ 17 ቀን በተለያዩ የማሊ አካባቢዎች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X