ቻይና የአፍሪካ ሀገራትን የወጪ ንግድ ዕድል የሚያነቃቃ የዜሮ ቀረጥ ስርዓት አስጀመረች
17:59 01.05.2026 (የተሻሻለ: 18:33 01.05.2026)

© и°ўзЋЇй©°
ሰብስክራይብ
ቻይና የአፍሪካ ሀገራትን የወጪ ንግድ ዕድል የሚያነቃቃ የዜሮ ቀረጥ ስርዓት አስጀመረች
ቻይና ከዛሬ ጀምሮ ከቤጂንግ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ካላቸው 53ቱም የአፍሪካ ሀገራት ለሚገቡ ምርቶች የዜሮ ታሪፍ (ከቀረጥ ነፃ) መብት በመስጠት፤ በቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ ስር የጋራ ልማት ቁርጠኝነቷን አጠናክራላች።
🟠 ይህ እርምጃ ሰፊውን የቻይና ገበያ ለአፍሪካ ላኪዎች በበለጠ ሁኔታ ክፍት የሚያደርግ ሲሆን በተለይም ቀደም ሲል ሙሉ በሙሉ ከቀረጥ ነፃ ዕድል የነበራቸውን 33 ታዳጊ ሀገራት በእጅጉ ይጠቅማል።
🟠 ለቀሪዎቹ 20 የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ እስከ እ.ኤ.አ 2028 ድረስ የሚቆይ የሁለት ዓመት የዜሮ ታሪፍ ስምምነት ተግባራዊ ይሆናል። ይህም የወጪ ንግዳቸውን ለመጨመርና ለማስፋፋት አዳዲስ ዕድሎችን ይፈጥርላቸዋል።
🟠 የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ ቻይና የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት አልማለች፦
▪ ከአኅጉሪቱ ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር፣
▪ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ዕድገት መደገፍ፣
▪ ለአፍሪካ ምርቶች የተረጋጋና የረጅም ጊዜ ገበያ ማቅረብ።
🟠 ተነሳሽነቱ በቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ ማዕቀፍ ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን እና የጋራ ብልጽግናን ለማጎልበት ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ አካል ነው።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X