ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች በሚስት የተቆረጠን ብልት በስፌት መለሱ

ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች
ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.05.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች በሚስት የተቆረጠን ብልት በስፌት መለሱ

በአሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በባለቤታቸው ጥቃት ደርሶባቸው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የወደቀው የ42 ዓመት ጎልማሳ እና የ6 ልጆች አባት ብልት፤ በአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተደረገ የ3 ሰዓታት ስኬታማ ቀዶ ህክምና ተመልሶ መገጠሙ ተሰምቷል።

ተጎጂው ጉዳቱ በደረሰ በ3 ሰዓት ውስጥ የተቆረጠውን አካል በፌስታል ጠቅልለው ሆስፒታል መድረሳቸው ለህክምናው ስኬታማነት ወሳኝ ነበር ተብሏል።

ብልቱ የመቆም እና የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የመፈጸም እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፤ እንደ ቀድሞው ሙሉ ጥንካሬ ላይኖረው እንደሚችል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

‍ ባለሙያዎቹ እንዲህ ዓይነት አደጋ ሲያጋጥም የተቆረጠውን አካል ሳይቆሽሽ በንጹህ ፌስታል በመጠቅለል ከ6 እስከ 8 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ህክምና ተቋም ማድረስ አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0