የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኦፔክ መውጣት በኋላ ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ አጋርነት መመስረት ትችላለች - ደቡብ አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ተንታኝ
16:29 01.05.2026 (የተሻሻለ: 16:34 01.05.2026)
ሰብስክራይብ
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኦፔክ መውጣት በኋላ ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ አጋርነት መመስረት ትችላለች - ደቡብ አፍሪካዊ የምጣኔ ሀብት ተንታኝ
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ሊደርሺፕ ካውንስል መስራች የሆኑት ፐርሲ ሞራፔዲ ኮጂ፤ ይህ ወቅት አፍሪካ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የጠበቀ የኢነርጂ ትስስር ለመፍጠር እና በአጠቃላይ በአኅጉሪቱ የንግድ ትብብርን ለማጎልበት ምቹ አጋጣሚ ነው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የባለሙያው ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ አፍሪካ ከዓለም ወጣቷ እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አኅጉር እንደመሆኗ መጠን የወደፊቷ የፍጆታ፣ የስርጭት እና የሽያጭ ቁልፍ ገበያ ናት፣
▪ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና የአፍሪካ የጠበቀ ትብብር ከኦፔክ ማዕቀፍ ውጭ የተረጋጋ እና የተመጣጠነ የንግድ ጥምረት ሊፈጥር ይችላል፣
▪ ይህ እርምጃ የአፍሪካ ሀገራት ቀጣናዊ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና የምርት ስልቶቻቸውን በበለጠ ነፃነት እንዲመሩ ዕድል ይከፍታል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኦፔክ እና ኦፔክ ፕላስ የመውጣት ውሳኔ ከአርብ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X