የአገው ፈረሰኞች በዓል በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ይሠፍራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
15:55 01.05.2026 (የተሻሻለ: 16:04 01.05.2026)
ሰብስክራይብ
የአገው ፈረሰኞች በዓል በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ይሠፍራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
የአገው ፈረሰኞች በዓል በዓለም አቀፍ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት የሚያስችለው ሰነድ ተጠናቆ ለተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት መቅረቡን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።
ክንውኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ጎብኝዎች ዘንድ ያለው ተወዳጅነት እየጨመረ መምጣቱ ለምዝገባው መፋጠን ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
⏳ በዓሉ እ.ኤ.አ በ2027 በሚካሄደው የዩኔስኮ መደበኛ ስብሰባ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ሚኒስትሯ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ፤ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ይህ ታሪካዊና ባሕላዊ እሴት ተጠብቆ እንዲቆይ በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው ማለታቸውንም የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X