የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቢያንካ ኦጁኩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ

ቢያንካ ኦጁኩ
ቢያንካ ኦጁኩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.04.2026
ሰብስክራይብ
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቢያንካ ኦጁኩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ

የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ፤ ዩሱፍ ቱጋር በጎርጎሮሳዊያኑ 2027 በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለማተኮር ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ሹመቱን አግኝተዋል።

🟠 ጠበቃ፣ ዲፕሎማት እና የቀድሞ የውበት ንግሥት የሆኑት ቢያንካ ኦዱሜግዉ-ኦጁኩ፤ እ.ኤ.አ በ1988 " እጅግ ውቧ የናይጄሪያ ሴት" ተብለው ከመመረጣቸውም ባሻገር፤ "ሚስ ኢንተርኮንቲኔንታል" ውድድርን ያሸነፉ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ናቸው።

🟠 በዲፕሎማሲው ዘርፍ፤ በስፔን እና በጋና የናይጄሪያ አምባሳደር በመሆን እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት የናይጄሪያ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን አገልግለዋል።

ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ በተጨማሪም፤ አምባሳደር ሶላ ኤኒካኖላይዬን ለሚኒስትር ዴኤታነት በእጩነት አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ቲኑቡ ሸመቶቹ የናይጄሪያን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ይበልጥ ውጤታማ እና ስልታዊ ለማድረግ ያለሙ እንደሆኑና ተሿሚዎቹም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን እንዲያራምዱ፣ ክልላዊ መረጋጋትን እንዲያሳድጉ እና የናይጄሪያውያንን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ እንዲሠሩ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0