ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰላምና ጸጥታ ም/ቤት ሊቀመንበርነቷ ለሆርሙዝ ሰርጥና ወቅታዊው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ሰላማዊ እልባት ጥሪ አቅርባለች

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነቷ ለሆርሙዝ ሰርጥ እና ወቅታዊው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ሰላማዊ እልባት ጥሪዋን አቅርባለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሚዲያ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


የቡሩንዲ እና የሞዛምቢክ መሪዎች በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ ”መሪዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት ኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት እያስመዘገበችባቸው ካሉ መስኮች ልምድ ለመቅሰም እና በሀገራቸው ለመተግበር የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈርመዋል” ብለዋል።


እንደ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገለጻ፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የተከናወኑ ቁልፍ የዲፕሎማሲ ሥራዎች በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ግንኙነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠበቁ ናቸው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0