የዲጂታል ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሥራዬን በብቃት እየተወጣሁ ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ሰብስክራይብ

የዲጂታል ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሥራዬን በብቃት እየተወጣሁ ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ተቋሙ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከተሰነዘሩበት የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች 99 በመቶ የሚሆኑትን ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ እንደቻለ አስታውቋል።

በተጠቀሰው ግዜ 50,155 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተሰንዝረዋል፣

ከዚህ መካከል ሰርጎ ገብ በ20,601 የጥቃት ሙከራዎች 41% በመቶ ይሸፍናሉ፣

በተጨማሪም በ338 ሲስተሞች ላይ የደህንነት ፍተሻ በማድረግ ተቋማት ለጥቃት የመጋለጥ እድላቸውን እንዲቀንሱ ተደርጓል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ትዕግስት ሃሚድ፤ “የሳይበር ደህንነት የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሉዓላዊነትና የብሔራዊ ደህንነት ዋስትና ነው” ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0