- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከመገኛነት ወደ ጠንካራ የምርት መለያነት፦ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአለም አቀፍ መድረክ

ከመገኛነት ወደ ጠንካራ የምርት መለያነት፦ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአለም አቀፍ መድረክ
ሰብስክራይብ
"የኢትዮጵያ ቡና ከሰራነው በላይ ፈጣሪ የሰጠን ትልቅ ሀብት ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ቡና ከአለም ቢጠፋ፣ ቡና ከአለም ላይ እንደሚጠፋ ያውቃሉ? ምክንያቱም የቡና ዝርያ ክምችቱና (Genetic Reserve) መሰረቱ ያለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የዋጋ አለመረጋጋት እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት እንዴት እያስተጓጎለ ይገኛል? ይህስ ለውጭ ምንዛሬ፣ ለኑሮ ሁኔታ እና ለገበያ መረጋጋት ምን ትርጉም አለው? በሚሉ ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ጋር የተወያየን ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት (UNHRC) በሩሲያ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ መሰረት አድርገን ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ከአቶ አንዱዓለም በውቀቱ ጋር የሰብአዊ መብቶች ስርዓት ስለተደቀነብት ፈተና ያደረግነውን ውይይት በሁለተኛው የመሰናዶአችን ክፍል አካትተነዋል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጃ ያድምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0