ፑቲን እና ትራምፕ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ተናገሩ
20:27 29.04.2026 (የተሻሻለ: 20:48 29.04.2026)

ሰብስክራይብ
ፑቲን እና ትራምፕ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ተናገሩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት፣ በድል ቀን የተኩስ አቁም ለማወጅ ዝግጁ መሆናቸውም ረዳቱ አክለዋል፡፡ ውይይቱ የተደረገው በሩሲያ ወገን አነሳሽነት ነው፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ስለ መሪዎቹ ውይይት ያጋሯቸው ተጨማሪ መረጃዎች፦
▪ ውይይቱ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ቆይቷል።
▪ ፑቲን፣ በትራምፕ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ በጽኑ ኮንነዋል፤ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
▪ የሩሲያ ፕሬዝዳንት፣ የኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት የማራዘም የትራምፕን ውሳኔ ትክክል መሆኑን ያምናሉ።
▪ ሞስኮ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ልታደርገው የምትችለውን የምድር ዘመቻ አደገኛ አድርጋ ትመለከተዋለች።
▪ ሩሲያ ከኢራን፣ ከባሕረ ሰላጤው አገራት፣ ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ንቁ ግንኙነት ትቀጥላለች።
▪ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለማቆም የሚደረገው ስምምነት አሁን ላይ መቃረቡን ያምናሉ።
▪ የሩሲያ ኃይሎች በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውስጥ የበላይነቱን በመያዝ የጠላትን ይዞታዎች ወደ ኋላ እየገፉ መሆኑን ፑቲን ለትራምፕ ገልጸዋል።
▪ መሪዎቹ፣ በዘለንስኪ የሚመራው የኪዬቭ አገዛዝ ግጭቱን ለማራዘም እየሠራ መሆኑን በተመለከተ ተመሳሳይ ግምገማ ሰጥተዋል።
▪ ፑቲን እና ትራምፕ የስልክ ቆይታቸውን በሞቅ ባለ ስሜት አጠናቀዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X