የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው" - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አማካሪ

ሰብስክራይብ
"የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው" - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አማካሪ

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ ሀገሪቱ ያላትን የኢነርጂ ሀብት በመጠቀም ከነዳጅና ከኢኮኖሚ ጥገኝነት የመላቀቅ ግብ ያለው መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አማካሪ አሰፋ ዐዲስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገለጹ።

ዘርፉን ለማሳደግ የሚወጡ አዳዲስ አሠራሮች ከመንግሥት ባሻገር የግል ባለድርሻ አካላትን ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው አማካሪው ይሞግታሉ።


“ስለዚህ የግሉ ዘርፍ በተለይ ደግሞ የዘርፉ መሪ ተዋናይ የሚባሉት እዚያው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የባለሀብቶችም ግለሰቦችም ለዚህ ዘርፍ እድገት ከፍተኛ የሆነ ሚና ይኖራቸዋል። [...] መሠረተ ልማቱ በሚገባ እስኪሟላ ድረስ አስመጪዎችም ሆኑ ተሽከርካሪ ገጣጣሚዎች የየራሳቸውን ሚና መጫወት መቻል አለባቸው።"


አሰፋ ዐዲስ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር፣ የባለሙያዎችን ክፍተት ለመሙላት በቻይና ሥልጠና ከመስጠት ባለፈ፣ ከአዲስ አበባ፣ ደብረ ብርሃን እና ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን አስታውሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0