92 የኤሌክትሪክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሥራ ጀመሩ – የኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

92 የኤሌክትሪክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሥራ ጀመሩ – የኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

እነዚህ ተሽከርካሪዎች በተለይ ለቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የ24/7 ግንባታ ሥራ እንዲውሉ በኮንትራክተሩ አማካኝነት የተገዙ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ተሽከርካሪዎቹ፣ በጥናት የተለዩ የደህንነት ችግሮችን የሚቀርፉና የጥራት መለኪያዎችን የሚያሟሉ፤ የተፈቀደላቸውን የጭነት መጠን ብቻ የሚጭኑ፤ 400 ኪሎዋት የባትሪ አቅም ያላቸው፣ የድምፅ ብክለት የማያስከትሉ እና የፍጥነት ገደብ የተገጠመላቸው በመሆናቸው ከአረንጓዴ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ጋር ይጣጣማሉ ብሏል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲስፋፋ ከፍተኛ የሆነ ርብርብ እየተደረገ መሆኑና የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ ተሽከርካሪዎች እና ቻርጅ ማድረጊያ ማሽኖች ከቀረጥ ነፃ መግባታቸውን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ እስከ 400 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገጣጥሙ 17 ተቋማት መፈጠራቸውም ይፋ አድርጓል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0