በኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 3 ሚሊዮን

ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 3 ሚሊዮን ወርዷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከሰብአዊ እርዳታ ጥገኝነት ነፃ እየወጣች፣ የመቋቋም አቅሟ እያደገ፣ በጠንካራ መሠረት ላይ እየተገነባች እንዲሁም ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውሶችን በስኬት እየተወጣች መሆኗን ‎”የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መድረክ ላይ በተሳታፊነት በሰጡት አስተያየት ላይ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ዓለም አቀፉ የነዳጅ ቀውስ፣ የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ ትራንስፖርት እና የአየር መንገድ አገልግሎቷ እንዳያቋርጥ ለማድረግን ባለፉት ሁለት ወራት ገደማ መንግሥት በነዳጅ ዘርፉ ከፍተኛ ድጎማ ማድረጉንም አክለዋል፡፡

ሕዝቡን ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ለመጠበቅ ሲባል በየወሩ እስከ 20 ቢሊዮን ብር የሚደርስ የነዳጅ ድጎማ ሲደረግ መቆየቱ የገለጹበትን ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አገርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0