በማሊ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አጠቃላይ በሳህል አገራት ኮንፌዴሬሽን ላይ የተቃጣ ነው - የጥምረቱ ፕሬዝዳንት
10:41 29.04.2026 (የተሻሻለ: 12:54 29.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በማሊ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አጠቃላይ በሳህል አገራት ኮንፌዴሬሽን ላይ የተቃጣ ነው - የጥምረቱ ፕሬዝዳንት
በማሊ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ማሊን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሳህል አገራት ጥምረት (ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር) ላይ የተቃጣ ነው ሲሉ የጥምረቱ የዚህ ዓመት መሪ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከፍተኛ ኪሳራ ለማድረስ እና ፍርሃትን ለማንገስ ታስቦ በተቀናጀ መልኩ በተለያዩ ቦታዎች ላይ መሰንዘሩን ገልጸዋል።
ሆኖም የማሊ ኃይሎች ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ጥቃቱን መመከታቸውን እና አሁን ላይ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን ትራኦሬ አክለው ገልጸዋል።
የሳህል አገራት ጥምረት ፕሬዝዳንት፣ የሳህልን የነጻነት ትግል በሚቃወሙ ጠላቶች የተጠነሰሰውን "አውሬአዊ ሴራ" የኮነኑ ሲሆን፣ ለማሊ አጋርነታቸውን ላሳዩ አጋሮችም ምስጋና አቅርበዋል።
የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ያጠናቀረው ቪዲዮ ከሚያዝያ 17 ጥቃት በኋላ በባማኮ ያለውን ድባብ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X