"ኢትዮጵያ ከባድ የጭነት የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስገባቷ ከቴክኖሎጂ ሙከራ ወደ ሥርዓት መር የኢኮኖሚ ሽግግር የማድረጓ ማሳያ ነው” – ባለሙያ
10:04 29.04.2026 (የተሻሻለ: 10:30 29.04.2026)

ሰብስክራይብ
"ኢትዮጵያ ከባድ የጭነት የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስገባቷ ከቴክኖሎጂ ሙከራ ወደ ሥርዓት መር የኢኮኖሚ ሽግግር የማድረጓ ማሳያ ነው” – ባለሙያ
ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን የምርትና አገልግሎት እንቅስቃሴ የሚሸፍኑት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ መቀየራቸው ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት እንደሚጥል የኤሌክትሪክ ሞቢሊቲ ባለሙያ እና አማካሪ በረከት ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
"የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብ ያስችለናል ... የኢትዮጵያ ኢነርጂ 90 በመቶው ከሃይድሮ ፓወር የሚመነጭ በመሆኑና በራስ አቅም የሚመረት መሆኑ የተረጋጋ የዋጋ ቁጥጥር እንዲኖረን ያስችላል" ሲሉ ባለሙያው የሀገር ውስጥ ኃይል አጠቃቀም ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል።
ባለሙያው፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ አቅም ለመጠቀም ኃይል በመሙያ ጣቢያዎች ላይ ሰፊ ኢንቨስትመንት ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
"የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ግብ ለማሣካት ቀረጥ ከማንሳት በተጨማሪ የተለያዩ ድጎማዎች መኖር አለባቸው" ብለዋል፡፡
በረከት ተስፋዬ፣ ከዚህ በተጨማሪ የባትሪ ደህንነት፣ የጥራት ደረጃ እና የአሠራር ሥርዓቶች መዘርጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X