በኢትዮጵያ የቀንድ ከብት ሀብት ላይ የተደረገ ጥናት የዝርያ ብዝሃነትን እና ዘመናዊ የማዳቀል አቅምን ይፋ አደረገ
19:04 28.04.2026 (የተሻሻለ: 19:56 28.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የቀንድ ከብት ሀብት ላይ የተደረገ ጥናት የዝርያ ብዝሃነትን እና ዘመናዊ የማዳቀል አቅምን ይፋ አደረገ
ከ70 ሚሊዮን በላይ የቀንድ ከብቶች ያሏት ኢትዮጵያ፣ ተወዳዳሪ የሌለው የሀገር በቀል ዝርያ ባለቤት መሆኗን በኢትዮጵያ ምሁራን የተሠራና "ባዩሎጂካል ዳይቨርሲቲ" በተባለ መጽሔት ላይ የታተመ ጥናት አመላከተ።
በጥናቱ መሠረት በሀገሪቱ ካለው የከብት ሀብት ውስጥ 97.4 በመቶ የሚሆኑት ሀገር በቀል ዝርያዎች ናቸው። እነዚህ ዝርያዎች ከተለያዩ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ጋር ያላቸው አስደናቂ የመላመድ ብቃት፣ በሽታንና ሙቀትን የመቋቋም ልዩ የዝርያ ባህሪ ያላቸው በመሆኑ ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ትልቅ ፋይዳ አላቸው።
ጥናቱ ዘመናዊ የዘረ-መል ማስተካከያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የወተት ምርትን ለማሳደግ እና ምርጥ ዝርያዎችን ለመለየት የሚያስችል አቅም መኖሩንም ጠቁሟል።
እንደ የመሠረተ ልማት እና የቴክኒክ አቅም ውስንነት ያሉ ተግዳሮቶች ዘርፉን ለማሳደግ እንቅፋት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ዘመናዊ ሳይንስን ከሀገር በቀል እውቀት ጋር በማቀናጀት የቀንድ ከብት ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ጥናቱ አሳስቧል።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X