ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የምዕራባውያን መጠቀሚያ ሆኗል - ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሎክ ኦቲየኖ ሉሙምባ
18:46 28.04.2026 (የተሻሻለ: 18:54 28.04.2026)

ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የምዕራባውያን መጠቀሚያ ሆኗል - ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሎክ ኦቲየኖ ሉሙምባ
ታዋቂው የሕግ ምሁር ፕሮፌሰር ሉሙምባ፣ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ነፃነቱን በማጣት የምዕራባውያንን ፍላጎት ብቻ የሚያስከብር ተቋም ሆኗል ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለማውጣት ሲሞክር በአሜሪካ በኩል የደረሰበት ተፅዕኖ፣ ተቋሙ ለአፍሪካውያንና ለምዕራባውያን ባላንጣዎች ብቻ ተብሎ የተቋቋመ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።
"የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ ሲወጣ፣ የአሜሪካ አስተዳደር ማዕቀብ ጥሏል፤ ምክንያቱም የእነሱ እይታ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የተቋቋመው አፍሪካውያንን እና እነሱ 'አስቸጋሪ' ብለው የሚፈርጇቸውን ሀገራት ለመቅጣት ብቻ ነው የሚል ስለሆነ ነው።[...] "በኔታንያሁ ወይም በአሜሪካ ባለሥልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ ለመውጣት ስትዝቱ፣ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ትችት፣ ስድብና መገለል ይደርስበታል።" ሲሉ ተቋሙ ከፍትሃዊነት ይልቅ አፍሪካዊያንን ማጥቂያ መሳሪያ መሆኑን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ ከ1945ቱ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር እና ከ1948ቱ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ በኋላ ስናውቀው የነበረው ዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ በአሁኑ ወቅት እየሞተ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X