አፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት "ስርዓታዊ ለውጥ" ልታደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
አፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት "ስርዓታዊ ለውጥ" ልታደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው 12ኛው የአፍሪካ ቀጣናዊ የዘላቂ ልማት ግቦች የግምገማ መድረክ ላይ፣ አኅጉሪቱ የ2030 እና የ2063 አጀንዳዎችን ለማሳካት ከተበታተነ አሰራር ወጥታ ወደ ስርዓታዊ አስተሳሰብ መሸጋገር እንዳለባት ተገልጿል።

የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቢና ናባንጃ የ2030 የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ዓመታት መቅረታቸውን በመጥቀስ፣ ውጥኖች በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲቀየሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው፣ አፍሪካ የፖሊሲ ሳይሆን የአፈጻጸም ችግር እንዳለባት ጠቁመው፣ በውጥኖቹ አፈጻጸምና አካሄድ ላይ “መሰረታዊ ለውጦች” እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።


አፍሪካ “ቁርጥ ያለ ለውጥ” የምትሻ ከሆነ በጊዜያዊ ውጫዊ ጫናዎችና መዋቅራዊ ችግሮች ሳትገታ፣ ከተበታተኑና ካልተቀናጁ አሰራሮች ወጥታ ስርዓታዊ አስተሳሰብን ልትገነባና ወደ ሰፊ የተግባር ምዕራፍ ልትሸጋገር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።


ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ በስድስት ዋና ዋና የዘላቂ ልማት ግቦች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0