ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ አዳዲስ የኃይል ማመንጫዎች ሥራ በመጀመራቸው የሀገሪቱ ኃይል የማምረት አቅም 9,730 ሜጋዋት ደርሷል -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
15:43 28.04.2026 (የተሻሻለ: 15:44 28.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ አዳዲስ የኃይል ማመንጫዎች ሥራ በመጀመራቸው የሀገሪቱ ኃይል የማምረት አቅም 9,730 ሜጋዋት ደርሷል -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ኃይል ወደ ማመንጨት መሸጋገራቸው ለዚህ የምርት እድገት አስተዋጻኦ ማድረጉን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ የተቋሙን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡
ግዙፉ የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለዋል።
በሌላ በኩል ለተቋሙ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት፣ ካለበት ከፍተኛ የዕዳ ጫና እንዲወጣ አስችለዋል ያሏቸውንም ጠቅሰዋል፦
🟠 የሀገር ውስጥ ዕዳ ወደ መንግሥት መዛወር፣
🟠 አዳዲስ ማመንጫዎች ሥራ መጀመራቸውና የኢነርጂ ምርት መጨመር፣
🟠 የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉ እና
🟠 የ"ዳታ ማይኒንግ" ሽያጭ በዶላር መከናወኑ ናቸው።
ይህ የገቢ እድገት እንደ ኮይሻ እና አይሻ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በራስ የፋይናንስ አቅም እንዲገነቡ አስችሏል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X