ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዘላቂ የመድኃኒት አቅርቦት ስርዓት እውን ለማድረግ እየሠራች ነው - ጤና ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዘላቂ የመድኃኒት አቅርቦት ስርዓት እውን ለማድረግ እየሠራች ነው - ጤና ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ የአፍሪካን የመድኃኒት ግዢ እና አቅርቦት ስርዓት ዘላቂነት ለማረጋገጥ እየሠራች እንደምትገኝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 5ኛው ዓለም አቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎች ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡


"ለአኅጉራችን የተሟላ የግዥ ሥርዓት ለመዘርጋት እየሰራን ነው። እራሳችንን እያዘጋጀን ያለነው ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለቀጣናችንም ሆነ ለአኅጉሪቱ አገራት ጭምር መግዛት እንድንችል ነው።" ብለዋል።


ለአቅርቦት ሰንሰለቱ ውጤታማነትም ከ3,500 በላይ የጤና ተቋማት በብሔራዊ የጤና መረጃ መረብ መገናኘታቸው መገለጹን ሁነቱን የታደመው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

የበለጠ ለማወቅ ተጨማሪ መረጃዎችን የያዘውን የስፑትኒክ አፍሪካ የቪዲዮ ጥንቅርን ይመልከቱ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0