የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ተጨባጭ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያሸጋግራል - ኢትዮጵያዊ ተንታኝ
12:31 28.04.2026 (የተሻሻለ: 13:29 28.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ተጨባጭ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያሸጋግራል - ኢትዮጵያዊ ተንታኝ
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ዘመን ለሞዛምቢክ የዋለችውን ውለታ ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሁም በፀረ ሽብር እንቅሰቃሴ ላይ የሚደረግ ትብብርን እንደሚያካትት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ መሐመድ ሲራጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እንደ ተንታኙ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ በኩል የታዳሽ ሃይል ማዕከል መሆኗ ሞዛምቢክ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ በኃይል ዘርፍ ያላቸውን ትብብር እንዲያሳደጉ ያገዛቸዋል፡፡
"አፍሪካውያን ሀገራት በኃይል ዘርፍ እርስ በእርስ መደጋገፋቸው ከምዕራባውያን ጥገኝነት ለመውጣት እጅግ በጣም ይረዳቸዋል። የእጅ አዙር የቅኝ አገዛዙንም ጭምር ለመፍታት ያግዛቸዋል፤ እስካሁንም ድረስ ያልተፈቱ በጣም በርካታ የቤት ሥራዎች አሉ፡፡"
ሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መስማማታቸው በተለይም ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው መሐመድ ሲራጅ አብራርተዋል፡፡
“ሞዛምቢክ በሰሜናዊ ግዛቷ በተለይ ካቦ ዴልጋዶ ከሚባሉ ጽንፈኛ ታጣቂዎች ጋር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጋፋች (እየተፋለመች) ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በሽብርተኝነት መከላከል ረጅም ልምድ ያላት አገር ናት፡፡ እናም የሁለቱ አገራት ግንኙነት የአኅጉሩ የጸጥታ ሥነ-ምኅዳር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ማሰብ ይቻላል ለማለት ነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ያደረጉት አቀባበል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X