- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከመረጃ-መር ፖሊሲ እስከ ሀገር በቀል ምርት:- የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንሳኤ

ከመረጃ-መር ፖሊሲ እስከ ሀገር በቀል ምርት:- የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንሳኤ
ሰብስክራይብ

"የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተመለከተ በህዝቡ ግንዛቤ ላይ ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል። የራሳችንን መለያ (Brand) ውብ ካደረግነው፣ የእኛ ምርት በአለም አቀፍ ገበያ ምርጡ መሆን ይችላል። ሁሉንም ነገር መጀመር ያለብን ሀገራችንን በመውደድ ነው፤ ለሀገራችን ውስጣዊ ፍቅርና ክብር ካለን፣ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን እናስባለን።" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና ተመራማሪ መሀመድ ኢሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን፤ በመጀመሪያው ክፍል የአፍሪካ ግብርና እና የፖሊሲ ምርምር የአፍሪካ የግብርና ፖሊሲ ምርምር ተቋማት መረብ (ANAPRI) ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንቶኒ ቻፖቶ፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ፣ የምግብ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የግብርና ስርዓቶች ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ ይሰጣሉ።
በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ ትኩረታችንን ወደ "Made in Ethiopia" ወይም "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አዙረን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪና አካዳሚሺያን ከሆኑት ከዶ/ር መሀመድ ኢሳ ጋር፤ የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሂደት፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ፋይዳ እና የሀገር በቀል ምርት መለያ (Branding) ስላለው ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ እሴት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0