በደቡብ ሱዳን ጁባ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ሰብስክራይብ

በደቡብ ሱዳን ጁባ አቅራቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

​የሀገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በዛሬው ዕለት እንደገለጸው፣ የአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች አውሮፕላኑ የተከሰከሰው እይታን በጋረደ መጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት ነው።

​በሲቲሊንክ አቪዬሽን የሚንቀሳቀሰው የሴስና 208 ካራቫን አውሮፕላን፣ ከዬአይ ወደ ጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየበረረ ባለበት ወቅት ግንኙነት መቋረጡን ባለሥልጣኑ በሰጠው መግለጫ አክሏል።

​በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካከል ሁለቱ የኬንያ ዜጎች ሲገኙበት የቀሩት ደግሞ ደቡብ ሱዳናውያን መሆናቸውን መገናኛ ግዙሃን ዘግበዋል። መረጃዎችን ለማሰባሰብ እና የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶችን ለመርዳት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን የአቪዬሽን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

ከጁባ ከተማ 20 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የአደጋው ስፍራ የተቀረጹ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የአውሮፕላኑ ቅሪቶች በእሳት ነበልባል ውስጥ ሆነው ያሳያሉ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0