ኢራን ባለሦስት ደረጃ የድርድር ማዕቀፍ ለአሜሪካ ማቅረቧ ተዘገበ
ኢራን በሦስት ደረጃዎች የሚከናወን የድርድር ረቂቅ ለአሸማጋዮች ማሳወቋ ተገልጿል። ዋሽንግተን የቀረበውን ሃሳብ የምትቀበል ከሆነ ቴህራን በዚያው መሠረት ድርድሩን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ፣ የቀረበው የድርድር ማዕቀፍ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካተተ ነው፦
ጦርነቱ በአፋጣኝ እንዲቆም ማድረግ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም በኢራን ወይም በሊባኖስ ላይ ዳግም ወታደራዊ ጥቃት ላለመሰንዘር ዋስትና መስጠት፤
ከግጭት ማግስት የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አጠቃቀምንና አያያዝን የሚመራ የሥራ ማዕቀፍ መዘርጋት፤
ስለ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር የሚነሱ ጉዳዮችን፣ በቀደሙት ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ብቻ እንደ የመጨረሻ ደረጃ ማየት።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X