የሩሲያ ጦር ኃይሎች የአፍሪካ ኮርፕስ በማሊ የተሞከረውን 'የሶሪያን አይነት መፈንቅለ-መንግሥት' ማክሸፉን አስታወቀ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ጦር ኃይሎች የአፍሪካ ኮርፕስ በማሊ የተሞከረውን 'የሶሪያን አይነት መፈንቅለ-መንግሥት' ማክሸፉን አስታወቀ

​የምዕራባውያን የመረጃ ድርጅቶች ሥልጠና የሰጧቸውና ቁጥራቸው ከ10 ሺህ እስከ 12 ሺህ የሚጠጋ ከፍተኛ ኃይል ያላቸው የ"አዛዋድ ነፃ አውጪ ግንባር" እና "አል-ቃይዳ በኢስላማዊ መግረብ"* የሽብር ቡድኖች ባለፈው አርብ በማሊ መፈንቅለ-መንግሥት ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውን ወታደራዊ ቅርንጫፉ ገልጿል።

​‍ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የዩክሬን እና የአውሮፓ ቅጥረኛ ተዋጊዎች በኪዳል እና ጋኦ ከተሞች አቅራቢያ በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት እና የጦር ክፍሎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች መሳተፋቸውን፤ ለጥቃቱም የምዕራባውያን ውጤት የሆኑትን "ስቲንጌር" እና "ሚስትራል" የተሰኙ ተንቀሳቃሽ የአየር መከላከያ መሣሪያዎችን መጠቀማቸውን ክፍሉ አመልክቷል።

አፍሪካ ኮርፕፕ፣ "በምዕራባውያን እና በዩክሬን አሰልጣኞች በሚመሩ የታጠቁ ቡድኖች የተቀናጀ ጥቃት በተሰነዘረበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ፤ የጥንቃቄ እርምጃ የወሰዱት ወታደሮቻችን እና መኮንኖቻችን ጠላት የመንግሥት ግልበጣ ለማድረግ የነበረውን እቅድ እንዲከሽፍ እና በአገሪቱ ያለው የመንግሥት መዋቅር የተረጋጋ እንዲሆን አስችለዋል" ብሏል።

ቪዲዮ፦ ባማኮ ከጥቃቱ በኋላ

* በሩሲያ እና በሌሎች አገራት የታገደ የሽብር ቡድን

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0