ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አመራሮች ጋር ተገናኙ፤ አጋርነታቸውን አረጋገጡ

ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አመራሮች ጋር ተገናኙ፤ አጋርነታቸውን አረጋገጡ
ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አመራሮች ጋር ተገናኙ፤ አጋርነታቸውን አረጋገጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.04.2026
ሰብስክራይብ
ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ አመራሮች ጋር ተገናኙ፤ አጋርነታቸውን አረጋገጡ

​የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭን እና ከሩሲያ ዱማ (የታችኛው ምክር ቤት) አፈ-ጉባኤ ቭያቼስላቭ ቮሎዲንን ጋር ፒዮንግያንግ ውስጥ በዛሬው ዕለት መገናኘታቸውን ኬሲኤንኤ ዘግቧል። ሁለቱም ወገኖች የተገናኙት በውጭ አገር ወታደራዊ ዘመቻዎች የጦርነት ገድል መታሰቢያ ሙዚየም ምርቃት ላይ ለመታደም ነው።

​ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያ ልዑካን ቡድን ጋር "ሞቅ ያለ እና ወዳጅነት የተሞላበት" ውይይት አድርገዋል። ከመሪው ቭላድሚር ፑቲን የተላከላቸውን ሰላምታ የተቀበሉ ሲሆን፥ ሞስኮ የአጋርነት ግንኙነቱን ለማጠናከር ላሳየችው ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

​ ኪም የሰሜን ኮሪያ እና የሩሲያ ኃይሎች የጋራ ትግልን ያነሱ ሲሆን፥ የኩርስክ ግዛትን ነፃ ለማውጣት በተደረገው ዘመቻ ሁለቱ ወገኖች "ጎን ለጎን ተሰልፈው በመታገል ድል ተቀዳጅተዋል" ብለዋል። ይህ ክስተት የአጋርነቱ ጥንካሬ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

​አክለውም፣ ሰሜን ኮሪያ "የሩሲያ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና የደህንነት ጥቅሟን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ" በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን፥ ሩሲያ ድል እንደምትቀዳጅም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0