ስለ ትራምፕ የእራት ግብዣ ጥቃት ፈፃሚ የምናውቃቸው ዝርዝር መረጃዎች
ፖሊስ እስካሁን ስለ ዋይት ኋውስ የጋዜጠኞች እራት ጥቃት አድራሽ ኮል ቶማስ አለን የስነ-ልቦና መገለጫ ለመስጠት ወይም ስለ ድርጊቱ መንስኤዎች ለማብራራት አልቻለም።
🟠 የ31 ዓመቱ አለን፣ ከምስጢራዊ ደህንነት አገልግሎት ጋር የተኩስ ልውውጥ በኋላ በቁጥጥር ስር ሲውል ምንሽር፣ ሽጉጥ እና በርካታ ቢላዎችን ታጥቆ የነበረ ሲሆን፣ "የመንግስት ባለስልጣናትን" ኢላማ ለማድረግ አቅዶ እንደነበር ተገልጿል።
🟠 ራሱን የቻለ የጨዋታ ሶፍትዌር አልሚ እና የምህንድስና ዳራ ያለው አለን፣ በቶራንስ ካሊፎርኒያ በሚገኘው ‘ሲ2 ኢዱኬሽን' የተባለ የግል የትምህርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ውስጥ በትርፍ ጊዜ መምህርነት እና ረዳት መምህርነት በመስራት ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2024 መገባደጃ ላይ ‘የወሩ ምርጥ መምህር’ ተብሎ ተሰይሞ ነበር።
🟠 ከዚያ በፊት፣ በ2020 ‘ሱ -ካም ኢንተለጀነት ኢዱኬሽን ሲስተምስ’ በተባለ ንቁ የመማር ማስተማር ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ ውስጥ፣ እንዲሁም በእ.ኤ.አ. በ2017-2018 መካከል በደቡብ ፓሳዴና በሚገኘው እና ወታደራዊ ግንኙነት ባለው ‘አይጄኬ ኮንትሮልስ' የተባለ የጂምባል አምራች ኩባንያ ውስጥ በሚካኒካል መሐንዲስነት ሰርቷል።
🟠 በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 ‘ፍሉድ ሲይንክሮኒ' በተባለ፣ በሰውነት ውስጥ የሚቀበሩ ጥቃቅን የሕክምና ማከፋፈያ ዘዴዎች ላይ ልዩ ትኩረት በሚያደርግ ተቋም ውስጥ በሰልጣኝነት አገልግሏል።
🟠 እ.ኤ.አ. በ2017 ከካልቴክ በሚካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 ደግሞ ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ዶሚንጌዝ ሂልስ በኮምፒውተር ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል።
🟠 በካልቴክ በነበረበት ወቅት የክርስቲያን ፌሎሺፕ፣ የኔርፍ እና የብሊትዝክሪግ ቦትስ የሮቦቲክስ ቡድን ክለቦች አባል ነበር።
🟠 በ2014 አለን በናሳ ጄት ፕሮፐልሽን ላብራቶሪ የክረምት የምርምር ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ በአስትሮፊዚክስ ጥናት ላይ ሰርቷል።
ትኩረትን የሚስቡ እና እንግዳ ዝርዝሮች፦
▪አለን እ.ኤ.አ. በ2024 ለካማላ ሃሪስ የፕሬዝዳንትነት የምርጫ ቅስቀሳ የ25 ዶላር እርዳታ ሰጥቷል።
▪ ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ የለበትም።
▪ አለን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት መለያ የለበሰበት ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ነው።
▪ መንግስት አልባነትን "አናርኪስት" የሚደግፍ አመለካከት እንዳለው ተገልጿል።
▪ የቀድሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቮሊቦል የቡድን አጋሩ ግለሰቡን "በጣም ረጋ ያለ"፣ "ገር" እና "ሊቅ ሊባል የሚችል" ሲል ገልጾታል።
▪ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና መርማሪዎች ድርጊቱን እንደ "ብቸኛ ተኩላ" ጥቃት እየተመለከቱት ይገኛል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X