በማሊ መጠነ ሰፊ የፀጥታ ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑን ጦሩ አስታወቀ

ሰብስክራይብ

በማሊ መጠነ ሰፊ የፀጥታ ፍተሻ እየተካሄደ መሆኑን ጦሩ አስታወቀ

​ በትናንትናው ዕለት በታጠቁ አሸባሪ ቡድኖች ጥቃት በተፈጸመባቸው በባማኮ፣ በካቲ እና በሌሎች አካባቢዎች መጠነ ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የማሊ የጦር ኃይሎች አስታውቀዋል።

​በጥቃቱ ሲቪሎች እና ወታደሮችን ጨምሮ 16 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን፣ የደህንነት ኃይሎች በርካታ አሸባሪዎችን በመግደላቸው በአሁኑ ወቅት ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን መንግስት ገልጿል።

​ በአሁኑ ወቅት በባማኮ እስከ ሚያዚያ 20 የሚቆይ ከምሽቱ 3:00 እስከ ረፋዱ 12:00 ሰዓት የሚዘልቅ እና በጋኦ ክልል ከምሽቱ 1:30 እስከ ረፋዱ 12:00 ሰዓት የሌሊት የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል። ባለስልጣናት እንደ አስፈላጊነቱ ሁለቱም የእገዳ እርምጃዎች ሊራዘሙ እንደሚችሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ከዚህ ክስተት በኋላ ዜጎች ለጦር ኃይሉ ያላቸውን የህዝብ ድጋፍ ሲገልጹ ታይተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0