ልዩ የማርሻል አርት እና የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ
12:19 26.04.2026 (የተሻሻለ: 12:24 26.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ልዩ የማርሻል አርት እና የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሄደ
በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የድብልቅ ማርሻል አርት፣ ሙአይ ታይ እና የቦክስ ፍልሚያ ትናንት ከቀኑ 10:00 ጀመሮ በአድዋ መታሰቢያ ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ በታልቅ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጆኒ እና የንቃተ ሕሊና የድብልቅ ማርሻል አርት ፍልሚያ ገና በመጀመሪያ ዙር በጆኒ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ ይህ ፍልሚያ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ልዩ ትኩረት አግኝቶ የቆየ ነበር፡፡ ባለድሉ ጆኒ የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በተጨማሪም፣ የድብልቅ ማርሻል አርት፣ የሙአይ ታይ እና ሦስት የቦክስ በድምሩ አምስት ፍልሚያዎች ተደርገዋል፡፡
ለተፋላሚዎቹ በአጠቃላይ እስከ 3.5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ከአዘጋጆቹ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ቪዲዮዎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia