የሩሲያ የሕዋ ባለሙያዎች የደቡብ አፍሪካ ጠፈርተኞችን ሊያሰለጥኑ ነው

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የሕዋ ባለሙያዎች የደቡብ አፍሪካ ጠፈርተኞችን ሊያሰለጥኑ ነው

​ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የጠፈር ኤጀንሲ እና ሩሲያ በጋራ የጠፈር ተጓዦች ማሰልጠኛ ፕሮግራም እንደሚጀምሩ የኤጀንሲው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሁምቡላኒ ሙዳው ለሩሲያ የዜና ማሰራጫ ተናግረዋል።

​ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን የጠፈር ተጓዥ እ.ኤ.አ. በ2027 ለጠፈር ተልዕኮ ለማሰልጠን ማቀዷንም ጠቅሰው ተናግረዋል።


የሩሲያ የጠፈር ኮርፖሬሽን (ሮስኮስሞስ) በበኩሉ፣ "በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ እና በተስማማንበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እጩዎችን በመምረጥና በማሰልጠን ረገድ ከደቡብ አፍሪካ አጋሮቻችን ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነን" ብሏል።


የሩሲያ ቀዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ማንቱሮቭ በሩሲያ የጠፈር ፎረም ላይ እንደገለጹት፣ ሩሲያ ከእስያ፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጋር ለጠፈር ተጓዦች ስልጠና እንዲሁም ለቴሌኮም እና ለመሬት ምልከታ ሳተላይቶች የሚሆኑ ውሎችን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

ቪዲዮው የአይኤስኤስ-75 ተጠባባቂ አዛዥ ዲሚትሪ ፔቴሊን ረጅም ጊዜ ለሚቆይ የስበት ጫና ያላቸውን የመቋቋም አቅም ለማረጋገጥ በ4ጂ እና 8ጂ ሴንትሪፊውጅ ሙከራዎችን ሲያልፉ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0