ኢትዮጵያ ልዩ የግብርና ምርቶቿን ጥራት ከፍ የሚያደርግ አዲስ የመልካ ምድራዊ አመላካች ሕግ ወደ ሥራ ልታስገባ ነው

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ልዩ የግብርና ምርቶቿን ጥራት ከፍ የሚያደርግ አዲስ የመልካ ምድራዊ አመላካች ሕግ ወደ ሥራ ልታስገባ ነው

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን እንደሚለው ማዕቀፉ እንደ የትግራይ ነጭ ማር፣ የሲዳማና ይርጋጨፌ ቡና ያሉ ምርቶች ከሚመረቱበት አካባቢ፣ የአየር ንብረትና የማምረት ሂደት ጋር ተያይዞ ላላቸው ልዩ ባህሪ ሕጋዊ ከለላ እና መለያ ይሰጣል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዳሉ ሞሲሳ፤ “ማሻሻያው ልዩ የሆኑ የሀገር በቀል ምርቶች በዓለም ገበያ ተገቢውን ዕውቅናና ጥበቃ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ ነው” ሲሉ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ተናግረዋል።

ሕጉ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀልና በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ውስጥ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ገልፀዋል።

ምዝገባ እና የጥበቃ ሥራው በቅርቡ ከምርምር ተቋማትና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር እንደሚጀመር ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0