ቡርኪና ፋሶ እስከ 2026 ድረስ 100 ሺህ ተጠባባቂ ወታደሮችን ለመመልመል 'ስልታዊ የመከላከያ ሰነድ' አጸደቀች
16:02 25.04.2026 (የተሻሻለ: 16:04 25.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ እስከ 2026 ድረስ 100 ሺህ ተጠባባቂ ወታደሮችን ለመመልመል 'ስልታዊ የመከላከያ ሰነድ' አጸደቀች
ረቂቅ ሕጉ አላባራ ያለውን የሽብር ስጋት ለመከላከልና የሀገሪቱን የጸጥታ ክፍተቶች ለመሙላት የሚያስችል ወታደራዊ ተጠባባቂ ኃይል ለመፍጠር ያለመ ነው።
አዲሱ ተጠባባቂ ኃይል ሁለት መዋቅሮች ይኖሩታል፦
🟠 በማንኛውም ጊዜ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ የቀድሞ የጦር ኃይል አባላት፣
🟠 ብሔራዊ መከላከያን ለማጠናከር ሥልጠና የሚሰጣቸው ሲቪሎች።
የኢብራሂም ትራኦሬ መንግሥት ሰነዱን ያጸደቀው ሲሆን ውይይት ተደርጎበት ወደ ሥራ እንዲገባ ለሀገሪቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተላልፏል።
ቪዲዮው የቡርኪና ፋሶ እና የኒጀር ወታደሮችን ወታደራዊ ትዕይንት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X