የግብፅ ፓርቲ መሪ አዲሱ ቅኝ አገዛዝ የታዳጊ ሀገራትን ሀብት ለመዝረፍ የሚጠቀምበትን ቀመር አጋለጡ
14:50 25.04.2026 (የተሻሻለ: 16:26 25.04.2026)

ሰብስክራይብ
የግብፅ ፓርቲ መሪ አዲሱ ቅኝ አገዛዝ የታዳጊ ሀገራትን ሀብት ለመዝረፍ የሚጠቀምበትን ቀመር አጋለጡ
ታላላቅ ኃይሎች የታዳጊ ሀገራትን የተፈጥሮ ሀብት በመቆጣጠር፣ ሀገራቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲበደሩ ተፅዕኖ በማሳደር የሚያሽመደምዱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በሀገራቱ ላይ ይጭናሉ ሲሉ የግብፅ ብሔራዊ ምክክር ፓርቲ መሪ መሐመድ ማሕሙድ ሪፋት ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እነዚህ ተቋማት የሚጠቀሙትን የሴራ ቅደም ተከተል አስቀምጠዋል፦
ቁልፍ የዓለም ኃይሎች የሌሎችን እድገት ለማቀጨጭ እና እንቅፋት ለመፍጠር የተለያዩ መሣሪያዎችን ይጠቀማሉ፤ ዓላማቸውም ሀገራቱን በዕዳ የተተበተቡ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
ይህም ሀገራቱ እንደ ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ወደመሳሰሉ ተቋማት እንዲያማትሩ ይገፋፋቸዋል። እነዚህ ተቋማት ገንዘብ ያቀርቡና የእርዳታ ፈላጊዎቹን ሀገራት ኢኮኖሚ በቁጥጥራቸው ስር ያደርጋሉ።
ሌላው የቁጥጥር መንገድ ደግሞ የየትኛውም ኢኮኖሚ መሠረት የሆኑትን የሀገራትን ሉዓላዊ ተቀማጭ ሀብት ማገት ነው። ይም ለኢኮኖሚ ውድቀት ብቻ ሳይሆን ለውጥረትና ለወታደራዊ ግጭቶች መንስኤ ይሆናል።
እንዲህ ያሉት እርምጃዎች አዲሶቹ የቅኝ አገዛዝ ኃይሎች የሀገራትን ሀብት ለመውረስና ሌሎችም የእነርሱን ፈር እንዲከተሉ ለማስገደድ ያስችላቸዋል።
ባለሙያው እንዲህ ዓይነቱ ፖሊሲ "በሀገራት እና በሕዝቦች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በመሆኑ፤ መብቱን ለማስመለስ የነቃ እንቅስቃሴ ያሻል" ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X