የኢትዮጵያ የመስኖ ልማት ሥራ ተስፋ እየታየበት እንደሆነ ተገለጸ
14:10 25.04.2026 (የተሻሻለ: 14:14 25.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የመስኖ ልማት ሥራ ተስፋ እየታየበት እንደሆነ ተገለጸ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ117 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማቱን ለተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡
ለፓርላማው የተቋሙን የሦስተኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ያቀረቡት ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ፤ 100 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ 117,100 ሄክታር መሬት ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።
ይህም የሀገሪቱ ዘመናዊ የመስኖ መሠረተ ልማት ሽፋን በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ከነበረበት 2.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከ2.6 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
ሚኒስትሩ በዘርፉ የታዩ ማነቆዎችንም በሪፖርታቸው አንስተዋል፦
የበጀት እጥረት፣
የጸጥታ ችግሮች፣
የፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናትና ዲዛይን ችግሮች ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች የመስኖ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ፣ ወጪ እና ጥራት ለማጠናቀቅ እንቅፋት በመሆናቸው ትኩረት እንደሚሹ አስገንዝበዋል።
ተንቀሳቃሽ ምሥሉ በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የተመረቀውን የቄጦ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X