የአፍሪካ የአቪዬሽን ደህንነት ቁጥጥር ደረጃ እያደገ መሆኑ ተገለፀ

አፍሪካ
አፍሪካ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.04.2026
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የአቪዬሽን ደህንነት ቁጥጥር ደረጃ እያደገ መሆኑ ተገለፀ

ባለፉት አምስት ዓመታት በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የአቪዬሽን ደህንነት ቁጥጥር ደረጃ ከ55.22 በመቶ ወደ 60.96 በመቶ ከፍ ማለቱን የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የ2025 ሪፖርት አመልክቷል።

እ.ኤ.አ በ2024 መጠናቀቂያ በአኅጉሪቱ የሚገኙ 15 ሀገራት ቢያንስ አንድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያቸው የአቪዬሽን ደህንነት ቁጥጥር ደረጃን እንዳለፈ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

እንደ ሪፖርቱ ገለጻ፤ ውጤታማ አተገባበርን* የሚያሳዩ የሀገራት ውጤቶች እንደሚከተለው ተሻሽለዋል፦

ኮትዲቯር፦ ከ79.84 በመቶ ወደ 93.89 በመቶ፣
ናይጄሪያ፦ 91.45 በመቶ (ከቅርብ ጊዜው ኦዲት በኋላ)፣
ሴኔጋል፦ ከ63.26 በመቶ ወደ 84.89 በመቶ፣
ሴራሊዮን፦ ከ16.03 በመቶ ወደ 72.66%፣
ጋቦን፦ ከ26.07 በመቶ ወደ 72.91 በመቶ።

*ውጤታማ አተገባበር የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በዓለም አቀፍ የደህንነት ቁጥጥር ኦዲት ፕሮግራሙ የሚጠቀምበት ዋነኛ የደህንነት መለኪያ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0