የኬንያ ፕሬዚዳንት በናይጄሪያውያን የእንግሊዝኛ ንግግር በማፌዝ ውዝግብ ፈጠሩ
10:20 25.04.2026 (የተሻሻለ: 10:24 25.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኬንያ ፕሬዚዳንት በናይጄሪያውያን የእንግሊዝኛ ንግግር በማፌዝ ውዝግብ ፈጠሩ
"አንድ ናይጄሪያዊ ሲናገር ብትሰሙ ምን እያለ እንደሆነ ግራ ያጋባችኋል። ለእንግሊዘኛው የእንግሊዝኛ አስተርጓሚ ያስፈልጋል" ሲሉ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በጣሊያን ለሚኖሩ ኬንያውያን ንግግር ሲያደርጉ ቀልደዋል።
ፕሬዝዳንቱ ኬንያ በዓለም "ምርጥ የሰው ኃይል" ሀብት ባለቤት ከሆኑ ሀገራት አንዷ እንደሆነች በመግለጽ ይህንንም በሥልጠና "ማብቃት" ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።
ንግግሩን ተከትሎ ናይጄሪያውያን እና ሌሎች አፍሪካውያን በኬንያው መሪ ላይ የአፍሪካን ሀገር አዋርደዋል የሚል ክስ እና ከፍተኛ ተቃውሞ ሰንዘረዋል።
የሩቶ አስተያየት ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑሁ የነዳጅ ዋጋ ቢጨምርም ናይጄሪያውያን "ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች የተሻለ ኑሮ" እንዳላቸው ከተናገሩ በኋላ የመጣ ነው። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚ፣ በዘመናዊ ባሕል፣ በስፖርት እና በፖለቲካ ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚታየውን ቀልድ የታከለበት የትስስር ገጾች እሰጣገባ በድጋሚ ቀስቅሶታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X