በኒጀር የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ከቀጣዩ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ሊቆሙ ይችላሉ - ሚኒስትር

ኒጀር፣ ፈረንሳይ
ኒጀር፣ ፈረንሳይ   - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.04.2026
ሰብስክራይብ
በኒጀር የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ከቀጣዩ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ሊቆሙ ይችላሉ - ሚኒስትር

ፓሪስ አካሄዷን ቀይራ የታጠቁ ቡድኖችን መደገፏን ካቆመች፤ በኒጀር የሚፈጸሙ ጥቃቶች ሊቆሙ እንደሚችሉ የኒጀር የሀገር ውስጥ እና የሕዝብ ደህንነት ሚኒስትር መሐመድ ቱምባ ለአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።


ሚኒስትሩ “ለምሳሌ አሸባሪዎቹን ከጀርባ ሆኖ የሚደግፋቸው ማን እንደሆነ በትክክል ማወቅ ከቻልን፤ የሽብር ጥቃቶችን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ይቻላል። በእኔ በኩል አሸባሪዎቹ በፈረንሳይ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ብዬ አምናለሁ። በቀጣዩ ዓመት በፈረንሳይ ምርጫ ይካሄዳል። የሚቀጥለው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት አሸባሪዎችን መደገፉን ይቀጥላል ወይስ ወደ ሌላ ጉዳይ ያዞራል? ያንን አላውቅም” ብለዋል።


ፈረንሳይ ከሁለት ዓመት በፊት ኒጀርን "ለማጥቃት ሞክራ" እንደነበር የገለጹት ቱምባ፤ አሁን ላይ ግን "የተወሰኑ የደህንነት መረጃዎችን ማግኘት ስላልቻለች" ማጥቃት አትችልም ብለዋል። ኒጀር ፓሪስ የስለላ መረጃዎችን እንዳታገኝ እና የፈረንሳይን ሲግናሎች ለማጨናገፍ እየሠራች መሆኑንም ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።

የኒጀር ፕሬዚዳንት አብዱራህማን ቲቺያኒ ቀደም ሲል ፈረንሳይ ሀገራቸውን ለማተራመስ እየሞከረች ነው ሲሉ መክሰሳቸው እንዲሁም በዋና ከተማዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቅርቡ በተፈጸመው የአማፅያን ጥቃት እጇ አለበት ማለታቸው ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0