በኬንያ 36 ሰዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን ማኮብኮቢያውን ጥሶ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባ

ሰብስክራይብ

በኬንያ 36 ሰዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን ማኮብኮቢያውን ጥሶ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባ

ኢቢቢ ኤር በተባለው የኬንያ አየር መንገድ የሚንቀሳቀሰው የኢምብራየር ጄት፤ 32 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ከናይሮቢ መነሳቱን የኬንያ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።

አውሮፕላኑ በማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ማኮብኮቢያውን ስቶ በመውጣት በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቁጥቋጦ ውስጥ ገብቷል።

ባለሥልጣኑ፤ "መንገደኞች እና የበረራ አባላትን በሰላም እንዲወጡ ተደርጎ በአፋጣኝ አስፈላጊው ድጋፍ ቀርቧል። በመንገደኞችም ሆነ በሠራተኞች ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም" ብሏል።

ℹ ከሶማሊያ እና ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘው የማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ፤ በዋናነት ለስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የሚላኩ ሰብዓዊ እርዳታዎችን እንዲሁም ለባለሥልጣናት እና ለነጋዴዎች የሚከራዩ በረራዎችን የሚያገለግል ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0