ወደፊት የሚቋቋመው የበሽታ ስርጭት እና ቁጥጥር ጥናት ማዕከል የሩሲያ-ኮንጎ የሳይንስ ትስስርን ያጠናክራል - ባለሥልጣን
19:39 24.04.2026 (የተሻሻለ: 19:44 24.04.2026)
ሰብስክራይብ
ወደፊት የሚቋቋመው የበሽታ ስርጭት እና ቁጥጥር ጥናት ማዕከል የሩሲያ-ኮንጎ የሳይንስ ትስስርን ያጠናክራል - ባለሥልጣን
በሩሲያ ማይክሮብ ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ኢካተሪና ናይዴኖቫ፤ የሩሲያ-ኮንጎ የኤፒዲሚዮሎጂ ጥናት ማዕከል ዋና ዓላማ "በኮንጎ የሚዘዋወሩ ተላላፊ በሽታዎችን ማጥናት እና የበሽታዎቹን መንስኤዎች መረዳት” እንደሆነና በሀገሪቱ የበሽታዎቹን ስርጭት ለመቀነስ እንደሚረዳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ሞስኮ መሰል ማዕከላትን በሌሎች ሀገራት በተለይም በጊኒ እና ቡሩንዲ ቀደም ብላ መክፈቷን የጠቀሱት ተመራማሪዋ፤ በዘርፉ ጥናት ያለውን ፋይዳ የሚረዱ ባለሙያዎች ባሉባት "ኮንጎ ውስጥም ማዕከሉን ለመክፈት ጊዜው አሁን ነው" ሲሉ በጉባኤው* ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል።
አክለውም ሁለቱ ሀገራት በዚህ ዘርፍ ረጅም የትብብር ታሪክ እንዳላቸው በማንሳት፤ በቼካፒካ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
*2ኛው የሩሲያ-አፍሪካ የተላላፊ በሽታዎች መከላከል ጉባኤ የተዘጋጀው በሩሲያ የጤና አገልግሎት አማካኝነት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X