የኢትዮጵያን የቡና ማሳዎች በአዲስ የሳተላይት መከታተያ ሥርዓት የመለየት ሥራ ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ቡና
የኢትዮጵያ ቡና  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የቡና ማሳዎች በአዲስ የሳተላይት መከታተያ ሥርዓት የመለየት ሥራ ሊጀመር ነው

ኢትዮጵያን ጨምሮ የታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ብሩንዲ እና ሩዋንዳ የቡና እርሻዎችን በሳተላይት እና በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የታገዘ የክትትል ሥርዓት ውስጥ ለማካለል የሚያስችል የ "የቡና ሽፋን አጋርነት" ይፋ ተደርጓል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ የቡና እርሻዎችን በመለየት የደን ጭፍጨፋን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ተብሏል።

ይህ ተነሳሽነት የአውሮፓ ኅብረት እ.አ.አ ከታህሳስ 2020 በኋላ በደን ምንጠራ በተመረቱ የግብርና ምርቶች ላይ እጥለዋለሁ ካለው የንግድ ገደብ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡

ሕጉ ውስብስብ እና የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው በሚል ትችት ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡ በተለይም ከ60 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ቡና ምርት ጫካን ተገን ያደረገና ይህም ለዘመናት የቆይ አሠራር ከመሆኑ አኳያ የሀገሪቱን ገበሬ እንሚጎዳ ሲነገር ቆይቷል፡፡

ኢትዮጵያ በዚሁ ሕግ ሳቢያ የቡና ገበያዋን ወደ ቻይና እና የመሳሰሉት ሀገራት ለማዛወር እንደምተገደድም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጠቁመዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ሕግ እ.አ.አ ከታህሳስ 30 ጀምሮ በትላልቅ ኩባንያዎች፤ ከሰኔ 30፣ 2027 ጀምሮ ደግሞ በአነስተኛ ኩባንያዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0