የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የጥቅምት 29 ሁከት ምርመራ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የሰላም ጥሪ አቀረቡ
17:20 24.04.2026 (የተሻሻለ: 17:56 24.04.2026)

ሰብስክራይብ
የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የጥቅምት 29 ሁከት ምርመራ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የሰላም ጥሪ አቀረቡ
የታንዛንያን የድህረ-ምርጫ ሁከት እንዲመረምር በፕሬዝዳንቷ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚሽን የደረሰበትን የጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። በቀድሞው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ መሐመድ ቻንዴ ኦትማን የሚመራው ይህ ኮሚሽን፤ ሁከቱ ድንገተኛ ሳይሆን መንግሥትን ለማዳከም ሆን ተብሎ የተቀናጀ እንደነበር ገልጿል።
ፕሬዚዳንቷ በሰው መጥፋት፣ ግድያና አፈና የተሳተፉትን ጨምሮ ሁከቱን ባቀዱ፣ በገንዘብ በደገፉና ባስተባበሩ አካላት ላይ ጥብቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ የሰው ሠራሽ አካላት ድጋፍ እና ማገገሚያ እንዲመቻች እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው አነስተኛ ነጋዴዎች ድጋፍ እንዲደረግ ተወስኗል።
ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ሀገራዊ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን እንዲቋቋም የተወሰነ ሲሆን የሪፖርቱ ግኝቶች ለሀገሪቱ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንደ ግብዓት እንዲያገለግሉ ታዟል።
ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ "እንዲህ ያለ ክስተት ዳግም እንዳይከሰት በጋራና በቆራጥነት መሥስራት አለብን" ሲሉ ታንዛንያውያን ለሀገራዊ አንድነትና ለዕርቁ ሂደት ስኬት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X