ጋና ሦስት ከቪዛ ነፃ የጉዞ ስምምነቶችን አፀደቀች
ስምምነቶቹ ማልዲቭስ፣ ዛምቢያ እንዲሁም አንቲጓ እና ባርቡዳን እንደሚያካትቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሙኤል ኦኩዴቶ አብላክዋ መናገራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ሚኒስትሩ፤ “ለጋና ፓስፖርት የላቀ ዋጋ እየሰጠን ባለንበት በዚህ ወቅት ተጨማሪ ከቪዛ ነፃ ስምምነቶችን መደራደራችንን እንቀጥላለን። በተመሳሳይ በጋና የፓስፖርት አሰጣጥ ዙሪያ የደህንነት ሥርዓቶችን እናጠናክራለን” ብለዋል።
ስምምነቶቹ የሦስቱንም ሀገራት መደበኛ፣ የሥራ እና የዲፕሎማሲ ፓስፖርት የያዙ ዜጎችን የሚመለከቱና እስከ 30 ቀናት ድረስ ያለ ቪዛ ለመቆየት የሚያስችሉ ናቸው።
መንግሥት ለአፍሪካውያን ተግባራዊ ያደረገው አዲሱ "የነፃ ቪዛ ፖሊሲ" ያለ ገደብ ወይም በቀጥታ ወደ ሀገር መግባት ያስቻላል ማለት እንዳልሆነ ሚኒስትር አብላክዋ አብራርተዋል።
“ነፃ ቪዛ ማለት አንድ አፍሪካዊ የቪዛ ክፍያ አይከፍልም ማለት ነው፡፡ የኢ-ቪዛ አሠራርን በቅርቡ ስንጀምር ግን ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ወዳጆቻችን ወደ 250 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ ይከፍላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X