ሩሲያ ለኮንጎ ያበረከተቻቸው ላቦራቶሪዎች ‘ሁሉንም የባዮ-ደህንነት መስፈርቶች ያሟሉ ናቸው’ - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለኮንጎ ያበረከተቻቸው ላቦራቶሪዎች ‘ሁሉንም የባዮ-ደህንነት መስፈርቶች ያሟሉ ናቸው’ - ባለሙያ

በሩሲያ ማይክሮብ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ሰርጌ ጎሉቤቭ፤ ላቦራቶሪዎቹ በዘመናዊ የምርመራ መሣሪያዎች ከመሟላታቸውም በላይ በኃይል (ኤሌክትሪክ) እና በውሃ አቅርቦት ረገድ "ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን የቻሉ" መሆናቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ኡርሱል ሮሜን ንጋንትሴል እንደዘገበችው፤ ላቦራቶሪዎቹ በኮንጎ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ የባዮሎጂ ባለሙያዎች ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሠሩ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው።

የሁለቱ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎች የምስክር ወረቀቶች የተሰጡት ረቡዕ ዕለት በብራዛቪል በተካሄደው ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ተላላፊ በሽታዎች ጉባኤ ላይ ነው። ጉባኤው የተዘጋጀው በሩሲያ የሸማቾች ጥበቃ እና ደህንነት ቁጥጥር አገልግሎት አማካኝነት ነው።

ሞስኮ እስካሁን በአጠቃላይ 20 ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎችን ለአፍሪካ ሀገራት እንዳቀረበች የሩሲያ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል።

አዲሱን የብራዛቪል እና ሞስኮ የጤና ዘርፍ ትብብር በተመለከተ የስፑትኒክ አፍሪካን የቪዲዮ ዘገባ ይከታተሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0